June 17, 2014

እኛና አብዮቱ በፍቅረሥላሴ ወግደረስ ሦስተኛውና የመጨረሻው ግምገማ፣ በታደለ መኩሪያ

እኛና አብዮቱ በፍቅረሥላሴ ወግደረስ
ሦስተኛውና የመጨረሻው ግምገማ፣
በታደለ መኩሪያ

እኛና አብዮቱ በፍቅረሥላሴ ወግደረስ ሦስተኛውና የመጨረሻው ግምገማ፣ በታደለ መኩሪያ

ከምዕራፍ 13-19 ወይም ከገጽ221-440 ያለውን እገመግማለሁ።
በምዕራፍ 13 በመጀመሪያው ገጽ ላይ ሰለ ድርጅትና ሰለአባላት በሰጡት ትንታኔ ልጀምር፤ “ምንም አደጋ የማይጋብዝ አስከሆነና አነስተኛ መስዋዕት እነኳን የማይጠይቅ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ብሎም መጠነኛ ጥቅም እነደሚያስገኝ ከታወቀ የፓርቲ አባልነትን ይወዱታል። በአጋጣሚ ግን በአባልነት የተሰባሰቡበት ድርጅት ከመንግሥት ጋር ቢቃቃር በሕብረት ቆመው ከመታገ
ይልቅ ይሸሹታል። በነፃነት መደራጀትን የሚከለክ
መንግሥት ፍፁም አምባገነንና ፀረ-ዲሞክራሲ ሰለሚሆን ተደራጅተው ለመታገ
የሚፈ
ጉ የነቁ ምሁራን ይታሠራሉ፣ ይገደላሉ፣ ይሰደዳሉ።ይህም ሆኖ ግን የሕዝብን መብት ለማስከበር ሲሉ በጣም ጥቂቶች ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው በህቡዕ ይደራጃሉ፣በህቡዕ ሕዝቡን ይቀሰቅሳሉ፣ለአመፅም ያነሳሳሉ፣ከፖለቲካው ሥራ አልፈውም የትጥቅ ትግ
ያካሂዳሉ።” የደራሲው ትንታኔ ከ1966 ዓም በፊት በሀገራቸን ምንም ዓይነት የተደራጀ የፖለቲካ ፓርቲ አለመኖሩን ለማሣየት በወቅቱ በካድሬዎችና በደር
አባሎች በሰፊው ሕዝብን ይቀሰቅሱበት የነበው ግባት ነው። ለደር
አባላት እናንተሰ ከየትኛው ትመደባለችሁ ሲባሉ መልሳቸው ‘ደም አደር’ ነበር፤ ሆኖም ግን ከ1966 ዓ ም በኋላ ብዙ ድርጅቶች ተመስርተዋል፤ ከትንታኔያቸው ሦስት ባሕሪያት እናያለን ፣ አደርባዮችን፣ አምባገነኖችንና ቆራጥ ታጋዮችን፤ ደራሲው ከዘረዘሯቸው ስድስት የፖለቲካ ድርጅቶች እርሳቸው አባ
የሆኑበት ድርጅት ሀገር አስተዳድሯል። ስለዚህ ሌሎቸን ድርጅቶቸ በልማቱም ሆነ በጥፋቱ ብዙም ድርሻ አልነበራቸውም፣ ደራሲው የጥፋቱ አካ
አድርገው ሰለአቀረቧቸ ትክክልኛውን ግንዛቤ መጽሓፉን ላነበቡ ሁሉ ለማቅረብ እሞክራለሁ፤ በወቅቱ የጠቀሷቸው ድርጅቶች እነዚህ ነበሩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፤የመላ ኢትዮጵያ ሶሾሊስት ንቅናቅ (መኢሶን)፤ወዝአደር ሊ
(ወዝሊ
)፤ማርኪሲስት ሌኒኒስት ሪቮሊሽነሪ ድርጅት (ማሌሪድ)፤አብዮታዊ ሰደድ (ሰደድ)፤የኢትዮዖጵያ ጭቁኖች አበዮታዊ ትግ
(ኢጭአት) ደራሲው ሰለ ኢሕአፓ የሰጡት ትንታኔ በእርግጥ ለወጣቱ ትውልድ ትክክለኛውን ታሪክ ለማስተማር ከተነሱበት ዓላማ ጋር ይጣጣማ
ወይስ አይጣጣምም እስቲ አብረን እንየው፤ ምዕራፍ 14ና ምዕራፍ 15 ባጠቃላይ የሚገልጸው ሰለኢሕአፓ ነው። ከገጽ 243 -333 ዘጠና ገጾቸን ይሸፍና
፤ እነደካርታ ጫወታ ማሸነፊያ ጆከር ወይም ሰበዝ ባብዛኛው የመጻፉ ገጾች ውስጥ ኢሕአፓ የሚለው ቃ
ተሰግስጓ
። ሰለ ኢሕአፓ ደራሲው ያቀረቧቸውን ኩነቶች በአምስት ከፍያቸዋለሁ፤ በቀላሉ እውነቱ የት እንዳለ ለማየት እንዲያስች
ነው።
አብዮተኞችን መግደል፣ ሴቶቸን ለሴተኛ አዳሪነት ማስኮብለል፣ የኤኮኖሚ አሻጥር፣ በደርጎቸ ውስጥ ሁከት መፉጠር፣ ሀገር ማስገንጠልና ከውጪ አገር መንግሥት ጋር ማበር ናቸው፤
አብዮተኞቸን መግደል፣ ከገጽ 275-296 ውስጥ 271 አብዮተኞች በኢሕአፓ መገደላቸውን እናያለን፣ ወደ ዝርዝሩ ከመግባቴ በፊት ደራሲው በገዛ ብዕራቸው ገጽ 84 ላይ የጻፉትን አብረን እንየው፣ አሸከሮች፣ ዘበኞች፣ገረዶች መረጃ ይሰጡናል፤ መሣሪያ፣ገንዘብ፣ንብረት ወደ ሌላ ቦታዎች ማሸሻቸውን ይጠቁሙናል፤ ‘እኛ እስከ ዛሬ የበይ ተመልካች ነበርን፣ ዕድሜ ለእናንተ እንጀራ ሊወጣልን ነው! ከእናንተ ጎን ተሰልፈን አቆርቋዦችን እንታገላለን፣ በማንኛው ጊዜ ትዕዛዝ ብትሰጡን ለመፈጸም ዝግጁ ነን! ከጅመሩ የምቀኞች አብዮት አስመስሎታል። ደር
ነጉሡን ለማውረድ፣ ስልሳዎቹን ለመግደ
፣ የመሬትን አዋጅ ለማወጅ ሕዝቡ ደገፈኝ ይ
የነበረው እነዚህን እያዳመጠ ነበር፡፡ እነርሱም ከነዚህ የተሻለ ግንዛቤ አልነበራቸው፤ ለሰፈርተኛው ኗሪዎች፡ ወፍጮ ቤት ተላላኪዎች፣ የድግስ እንጨት ፈላጮች፣ ጌሾ ወቃጮች፣ ውለው አድረው፣ ለቀበሌ ሊቀመበርነት ለአብዮት ጠባቂነት በየመሥሪያ ቤቱም የተሰገሰጉት ይህ መሰ
ሰዎች ነበሩ። በቀበሌዎች ተመርጠው አባወራውን በአቆርቋዥ ስም አሣስረው፣ ልጆቻቸውን በኢሕአፓ ስም ጦቁመው ከቀድሞ እመቤቶቻችው ጋር አልጋ ልውጣ ሲሉ ዝም ማለቱ ይበጅ ነበር ነው የሚሉት? የቤተሰባቸው ጥቃት የተሰማቸው ልጆቻቸው ለመበቀ
የቀበሌውን ተመራጭ ተኩሰው ቢገድሉት ተጠያቂው ማነው? ሀገር እመራለሁ የሚለው መንግሥት ሀገሪቱን ሕ
አልባ አድርጎ፣ የዜጎችን ደህንነት ከማስጠበቅ ይልቅ ራሱ ገዳይ ከሆነ፣ ተጠያቂው ማነው? ሌላው ደግሞ የኢሕአፓ መፈክር የሆነውን ‘ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ይቋቋም’ በማለት ለሕብረተሰቡ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በህቡዕ፣ ወረቀት ሲበትኑ የያዟቸውን ወጣቶች ሲገርፋቸውና ሲያጉሏሏቸው ፣ ከዚህ እንዲታቀቡ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተልኮላቸው አሻፈረኝ ብለው ጥቆማውንም ግድያውንም በማንአለብኝ የገፉትን፤ በመግደላቸው የተሾሙትን፣ ከጥቆማም አልፎ ‘ነፃ እርምጃ’ የወሰዱትን፣ ኢሕአፓም ባሰማራቸው እስኳዱ አባላቱን ባስገደሉበት ግለሰቦች ላይ ግድያ ፈጽሟ
፤ ደራሲው ትንሸ ሚዛናዊ ለመሆን እንኳን አንድም በመንግሥታቸው ታጣቂዎች የተገደለ የኢሕአፓ አባ
ስም አልጠቀሱም፤ ቢፈልጉ የስም ዝርዝራቸውን ከየቀበልዎች ማግኝት ይችሉ ነበር፤ ኢሕአፓ የገደላቸውን በሺዎች ብለው ከጠቀሱት የ271 ዱን በዝርዝር ሲያቀርቡ ማለቴ ነው። የከፍተኛ 12 ኗሪው ብረሃኑ ሙሉጌታ ሃያ አራት ንጹሃን መግደሉን ገጽ 274 ገልጸዋል፤እዚህ ላይ ሰለድርጅቱ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እንደሌላቸው አያለሁ፤ ሁለት መረጃዎችን ልስጥ፣ በድብደባ ብዛት ወጣቱ ከዚያም በላይ ገደልኩ ሊ
ይችላል፣ ሁለተኛ የ አንድ የቀበሌ ሊቀመበር ሲገደ
በክፍተኛው ባሉ ቀበሌዎች በሙሉ ከታሰሩት ውሰጥ ቀደኛ ኢሕአፓ አባ
የሟላቸውን በድብደባ ገለና
አሰኝተው ይገሏቸዋል፤ በመፍክራቸውም አስቀምጥውታል፣ ‘አንድ አብዮተኛ ቢሞት በሺ ፀረ-አብዮተኛ’ በማለት ተፎክሯ
፤ ደራሲውም ‘ዲሞን በዲሞፍትር’ ሲሉ ገልጽውታል፣ይህ ወጣት አንድም ገደለ፣ ሃያም ገደለ፣ ወረቀት በተነ፣ ሞት አይቀርለትም፤ ሰለዚህ ሌሎች ጓዶችን ለማዳን ከጠቀሱት ቁጥር በላይ ገድያለሁ ሊ
ይቻላል፤ ሰለ ድብደባ ከተነሣ ያየሁትን ልናገር፣ ከፍተኛ ሃያ ፔፕሲ ማዞሪያ የኤልትክ ዕቃዎች መለዋወጫ መጋዘን የነበርው የከፍተኛው ሃያ እስር ቤት ውሰጥ አንድ ወጣት ሲደበደብ ቤታችን ውስጥ አልጋው ሥር ታንክ ተቀብሯ
ማለቱን በውቅቱ በአካባቢው በሰፊው ይወራ ነበር፤ ከዚህ የምረዳው የድርጊቱን ኢሰዕባዊነት ነው ። ይህም የሆነው የካቲት 1970 ዓ ም ነበር፤ ሌላው ደግሞ በገጽ 274 ላይ የ12 ዓመት ሕፃን ኢሕአፓ የላከው፣ ሰው ገድሎ እማማ ብሎ አለቀሰ ብለዋል፣ ፣ ለባብሌ ቶላ ግድያ ማስተባበያ እንደሆነ ግልጽ ነው። ፤ ደር
ሕፃኑን ባብሌ ቶላን የኢሕአፓ አባ
ብሎ በገደለበት ወቅት ትልቅ ተቃውሞ አስነስቶበት ነበር፤ ኢሕአፓም የደርግን ማንነት ለማጋለጥ ትልቅ የፖለቲካ ቅስቀሳ ሰርቶበታል። በገጽ 270 ላይ ስለርዕሰ መምህሩ ፍቃዱ ኡርጋ አገዳደ
የተረኩት ትረካ በፍጹም በማንም ሕብረተሰብ ውስጥ የሚደረ
አይደለም፤ አቶ ፍቃዱን ለማስገደ
በር ያስከፈተቻቸው ጎረቤታቸው በግ
ለኢሕአፓ ትተባብራለች እንበ
ግን ቤተሰቧ ላይ መነግሥት የሚወስደውን እርምጃ አታውቅም ማለት ይቻላ
? በዚያ ላይ ቤተሰቧና ሕብረተሰቡ እንደሚቃቃር እያወቀች በገሃድ በር አስከፍታ ጎረቤቷን አታስገድልም፤ ይህ ይሆና
የሚ
ካለ የራሱ ግንዛቤው ነው፣ ደራሲውም ግንዛቤያቸው ያ ነው፤ ? እውነት ከሆነ የአቶ ፍቃዱ ሞት ያሣዝናል፤ ደራሲው እንዲህ ልባቸው ለሰው ልጆች የሚደማ ከሆነ ’ ነፃው እርምጃ’ እየተባለ ለሚጠራው የግድያ ተግባር ያሰማሩት አረመኔው ግርማ ከበደ የብረሃነና ሰላም ማተሚያ ቤት ሠራተኛ የነበረችውን ነፍሰ ጡር ዳሮ ነጋሽን መግደሉን እንዴት ረሱት? የአዲስ አበባ ሕዝብ አይረሳውም፣ በወቅቱም ድፍን የአዲስ አበባ ሕዝብ ሰምቶት መንግሥታቸውን በመቃወም ሰላማዊ ሰለፍ ወጥቶ ነበር፣ እንጦጦ ያውም ሌሊት በመምህር ፍቃዱ ኡርጋ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በዝርዝር ሲያቀርቡት፣ በጠራራ ፀሐይ አራት ኪሎ ከመሥሪያ ቤታቸው በራፍ በዳሮ ነጋሽ ላይ የተፈፀመውን ግድያ አልሰሙትም፤ በወቅቱ ሕብረተሰቡ በግለጽ የሚያውቀውን ክዶ የእኔን ዕወቅልኝ ቢሉት አያዳምጥም፣ በመጸሐፉ ውስጥ የተገለጹት ኩነቶች ከምር ለመውሰድ ይጠራጠራል፡፡ ከግድያው ጎራ ሳልወጣ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ከሐምሌ 1969-1971 ዓ ም የነበረውን ሁኔታ በወፍ በረር መልክ ላሳያቸሁ፣ በሃያ አምስቱ ከፍተኞች፣ ከዘጠና የማያንሱ ቀበልዎች ውስጥ በኢሕአፓ የተጠረጠሩት እንደ ድርጊታቸው ክብደት ይታሰራሉ፤ እነዚህ ተጠርጣሪዎች በድብደባ የገደሉም ያልገደሉም ገለና
አሰኝተዋቸው በታይፕ በተፃፈ ሰነድ ላይ ያስፈርሟቸዋል፤በሌላ ቀበሌ የተገደለ የቀበሌ ሊቀመበር ወይም አብዮት ጠባቂም ከኖረ ባልነበሩት አካባቢም ቢሆን ገድያለሁ ብለው እንዲፈርሙ ይደረጋሉ፣ ወጣቶቹን ለአራት ለአምስት ጊዜ ካሰቃዩአቸው በኋላ ነው ገድያለሁ ብለው የሚፈርሙት፣ ሌላ ጠቋሚ ካልመጣ ይህንን ሁሉ ሥቃይ ተቋቋመው የሚድኑም ፣ የሚገደሉም ነበሩ፤ ገዳዮቹ ሌለት በስምንት ሰዓት ላይ በጫት መርቅነው፣ በመጠጥ ሰክረው ይመጣሉ፣ በመጋቢት ወር 1970 ዓ ም በከፍተኛ ሃያ ቀበሌ 40 ነበር። ሃያ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ውስጥ አሥራ ሁለት ወጣቶችን ለመግደ
ይወሰዳሉ፣ ገዳዮቹ የአባቶቻቸውን ስም ባላስታውስም፣ ፍሬው፣ ማስረሻ፣ እና ገበረመድህን ይባላሉ፡፡ የከፍተኛውን ካድሬ ስም ተዘነጋኝ፣ የከፍተኛ ሁለትና የከፍተኛ ሃያ ካድሬ ነበር። ግድያው ከቀበሌው አጥር በር ላይ ተጀመረ፤ ቸሩ ነበር፣ የተገደለው፣ ቸሩ የኮከበ ጸባሃ ሁለተኛ ደረጃ መምህር ነበር፣ ለማንበብ መጽሐፍ ካነሣ ገጾቹ ቢበዙም በአንድ ቀን ፉት ይለዋል፤ ከመገደሉ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ዓለም አቀፋዊ የሴቶች ቀን (March 8) ለማክበር ሴቶች እህቶቻችን በዐሉን የሚመለከት ጽሑፍ እንዲዘጋጅ ጠየቁ፤ እኔና ቸሩ ሐላፊነቱን ወስደን ሰለነበር ሰለሕብረተሰባችን እጅ
የታመቀ ዕውቀት እንዳለው የተረዳሁት ያኔ ነበር፣ ‘ድርብ ጭቁኗ’ በሚ
ርዕስ በድራማ መልክ አዘጋጅቶ፣ በምን ይታጀብ ሲባ
? ቸሩ ጊዜ አለወሰደበት ‘አምጭልኝ እህቴ’ የሚ
ግጥም ጽፎ ዜማ አወጣለት፤ ሁሉንም ሥራ ያቀነባበረው ቸሩ ነበር ። አራቱ ሴቶችና ስድስት ወንዶች ተሳታፊ ሲሆኑ የቀረነው ተመልካች ሆንን፤ ደራሲው ሰለድርጅትና አባላት በሰጡት ትንታኔ ውስጥ ሰለንቁ ምሁራን የሰጡትን ትንታኔ ቸሩ ያሟላዋ
እላለሁ፤ ቸሩ ለመገደ
ሲወጣ አንዱ ገዳይ የለበሰከውን ኮት አውልቅ ሲለው ‘ለሀገሬ ከዚህ የተሻለ ነገር ትቼላት የምሄደው ይኖኝ ይሆን? አወልቃለሁ፣’ የመጨረሻዋ ቃሉ ናት፤ የተገደለው በእውቀቱ ልቆ በመገኘቱ ብቻ ነበር። አሥራ አንዱ እጃቸው እንደታሰረ በአውራ መንገዶች ላይ በጥይት ተደብድበው ተገደሉ።
ኢሕአፓ ሴቶቹን ለሴተኛ አዳሪነት ማሰማራቱንና ማስኮብለሉን፣ ከገጽ 257-258 ታገኙታላችሁ፣ ደራሲው ኢሕአፓ ያልደረሰበት የሕብረተሰቡ ክፍ
እንደሌለ በሰፊው በመጻፋቸው ውስጥ ገልጸውታል፤ ሰለዚህ የቡና ቤት ሠራተኞችን፡ ወጥ ቤት ሠራተኞችን፣ አልጋ አንጣፊዎችን፣ ዘበኛዎችን፣ መጠጥና ምግብ አቅራቢ ሴቶችንም እንደማንኛው ሰው እኩ
መብት እንዳላቸው አስተምሯል፤ ይህን ያስተምረ ድርጅት ሴቶችን ለገንዘብ ለወሲብ ሥራ አሰማራ ሲሉ በማስረጃ አስደግፈው አይደለም፡፡ ኢሕአፓም ሆነ ሌሎቹ ግራ ዘመም ድርጅቶች በሴቶች መብት ጥያቄ ላይ የማያወላው
አቋም አላቸው። በሃምሣዎቹ ለሸቀጥ ማራገፉያ ለባህ
ብረዛ ሴቶችን ሚኒሰከርት የሚባለው ቀሚስ አልብሰው የፋሺን ሾ ተብሎ በጊዜው የቀዳማዊ ሃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሲቀርብ ተማሪዎች ያስቆሙት በገማ ዕንቁላ
በመዋጋት ነበር፣ የዚያ ትውልድ አካ
የሆነውን ኢሕአፓን ሴት ጓዶቹን ለወሲብ አሰማራ ብለው እንደ (pimp) መቁጠሩ፣ ውኃ አያነሣም፤ በኢሕአፓና በደር
መካከ
የማይታረቅ ቀራኔ ቢኖርም በመጽሐፍ መልክ አንድን ድርጅት ለማጋለጥ ሲባ
ቆራጥ ሴቶች የዋሉበትን ውሎ አፈር አልብሶ ለወሲብ ተሰማሩ ማለት በጣም ያሣፍራ
፣ የወሲቡ ጉዳይ ከተነሣ ከ66 አብዮት እሰከ 1972 ዓ ም ባሉት ዓመታት መካከ
የወጣቱ አዝማሚያ ምን ይመስ
ነበር? ከ1972ዓ ም ኢሕአፓ የከተማውን የፓለቲካ እንቅስቀሴ ካቆመ በኋላስ ? ይህንን የሀገሪቱ ዜጎች ይፍረዱት፤ አሁን በአለም ዙሪያ በሴት እህቶቻች ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ ደራሴው ይመሩት የነበረው መንግሥት ጥንስስ ነው፤ ሌላው ቀርቶ መንግሥት አለን ብለው የሀገር ሕልውና ለማስከበር በጅግንነት የሞቱ ጅንራሎችና ባለሌላ ማዕረ
ወታደሮች ልጆች በየበረሃው ተደፍተው ቀርተዋል፣ ውጭ አገር የወጡትም ቢሆኑ ያለፉበት ሰቆቃ ሁኔታ ብዙም በሕይወት እንዲኖሩ አላደረጋቸውም፤ በደራሴው ጠቅላይ ሚንስትርነት የታየው፣ የደር
አባሎችና ካድሬዎቻቸው በአዲስ አበባና በየክፍለሃገራት በሴቶች ላይ የፈጸሙትን በደ
ለመግለጸ መጽሐፍ ያጽፋል። በገደሏቸው ሹማምቶች ቤተሰብና ሴት ልጆቻቸው ላይ ያደረሱትን ሆድ ይፍጀው፣ ድፍን ያአዲስ አባባ ሕዝብ የሚያውቀውን’ ‘አረመኔው ግረማ ከበደ’ በሎ ሰም ያወጣለትን ነፍስ ገዳይ በመጽሐፋቸው ያላወጡ፣ ጓዶቻቸው በሴቶች ላይ ያደረሱትን በደ
ይጽፋሉ ብዬ አልጠብቅም። ምክንያቱም ባጠቃላይ አቀራረባቸው ሚዛኑን ያልጠበቀ፡ የኢትዮጵያዊነት ጨዋነት የጎደለው ነው። ኢሕአፓ የፖለቲካ ድርጅት ነው፤ የራሱ የሆኑ ብዙ ሰህተቶችን ፈጽመሟል፤ በሀገራችን በግለጽ መነጋገሩ ቢኖር ኖሮ አፍረጥርጠን የሁሉንም ወገን እናየው ነበር፤ሆኖም ኢሕአፓ የመንግሥት ሥልጣን አልያዘም፤ በትግሉ ግን የሴቶችን ድረብ ጭቆና ተቀብሎ በተግባር አውሏል፣ ድርጅቱን ጭላት እቀባለሁ ብለው ማስረጃ ለማያቀርቡበት ጉዳይ የታጋይ ሴቶችን ሰም ማጉደፉ ለማንም አይበጅም። ‘ለሴተኛ አዳሪነት በጎረቤት አገሮች አሰማራ፣’ ሲሉ፤ ከየትኞቹ የጎረቤት አገሮች? ሰውዬው ያለው ነገር መጣ፣ ‘ዋሽ
ኝ እዋሻለሁ ነፋስ በወጥመድ እይዛለሁ፤’ ይመስላል፤
ኢሕአፓ በኤኮኖሚው መሰክ የፈጸመውን አሻጥር እንየው፣ በመንግሥት እርሻዎችና በመገልገያ መሣሪያዎች ላይ ያደረሰውን ውድመት ገልጸዋል፣ የመንግሥት እርሻ የሚባ
ነገር የለም፤ ከመሬት አዋጅ በፊት ትልልቅ እርሻዎቸ የግለሰቦች ነበሩ፤ ሰለተወረሱት ሰፋፊ እርሻዎች የሚያወሩ ከሆነ መሬት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ሲው
እርሻ መሆኑ ቀርቶ ያደረ ማሳ ነው የሚሆነው፤ ለዚህ ተጠያቂ የሚሆነው ያለ ዕቅድ የሚሰራው መንግሥት ብቻ ነው። የሀገር ንብረት መውደም የመሬቱ ማደር ያሰቆጫቸውና አንድ ነገር እናድር
ብለው ነጋሸ ሣህሌ ከአጋርፋ ባሌ፣ ታደሰ ይርገጤ ዶዶላ ባሌ ይነሣሣሉ፤ ሁለቱም የኢፒድ ሠራተኞች ነበሩ፤ የማሳው ማደር የትራክተሩ መውደም የሚመለከትው የእርሻ ሚኒስትር ተወካዮችን ነበር፤ የስዊድን መንግሥት ለኢፒድ በሚልከው ባጀት ሠራተኞቹን አሰተባብሮ የተወረሰውን ማሳ በተወረሱት ትራክተሮች አርሶ ስንዴ ዘራው፤ ይህን ያደር
የነበረው ከካድሬዎች በመሸሸ
ነበር፤ 200000 ኩንታ
ስንዴ አምርቶ ከማጋዘን አግብቶ ለቤሔራዊ ሐብት ልማት አሰረከበ። ባሌ በክረምት መንገዱ አስቸጋሪ ሰለሚሆን ባአስቸኳይ እንዲያጓጉዙ ነግሯቸው ተመለሰ፤ አስር ሺ ኩንታ
በማጋዘኑ ቀርቶ ስለነበር በፍሳሸ ጥቂት ኩንታ
ይበላሻል፤ ገበሬዎች ይህን ስንዴ ከሰብ
በኋላ ሊተኩለት ለዘር ይጠይቁታል፣ በራሱ ለገበሬዎቹ መሰጠቱ ያስጠይቀኛ
በማለት በአካባቢው የደር
አባሉ ይመጣ
ሰለሚባ
ሲመጣ ጠይቁት ይላቸዋል፣ የደር
አባሉ ይመጣ
ይጠይቁታል፣ ማነው ያስቀመጠው ይላ
ነጋሸ ነው ይሉታ
፤ በ1968 ዓ ም ክረምት ላይ በባሌ ክፍለሃገር ኢሕአፓ የኤኮኖሚ አሻጥር ሠራ ተብሎ በቴሌቭዥን በተደጋጋሚ ለአዲሰ አበባ ሕዝብ ቀረበ፤ ነጋሸ ሣህሌ በኢሕአፓ አባልነት በኤኮኖሚ አሻጥረኝነት ታሰረ፤ ደራሲው ገጽ 315 ላይ የእርሻ ሚኒስትሩና የቤሔራዊ ሐብት ልማት ሚኒስትሩ መታሰራቸውን ገልጸዋል፤ መንግሥቱም ይህን ያልተጣራ ነገር ይዞ ቡራከረዩ ሲ
እነ መቶ አለቃ አለማየሁ ኃይሌ ጅንራ
ተፈሪ ባንቴም ቁም በአንደኛ ብለው ሥልጣኑን የተፈታተኑበት መነሻው ያ ነበር። ነጋሽ መን
ሥትን ቤሳ ቤቲን ሳያስወጣ ላመረተው ምርት ማስረጃዎቹን ቢያቀርብም ሊቀበሉት አለፈለጉም፤ ለእውነት ብሎ የቆመ አልነበረም፤ ነጋሸ አሥራ አራት ራሱን በአንድ ጉድጓድ በጥይት ተደብድበው ተገደሉ፣ አንዱ አብረው የተገደሉት፣ የሐረር ሕዝብ እንደራሴ ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ፣ ወንድም ናቸው፣ የታወቁ አርበኛ ነበሩ፣ ሃይሌ ዘለቀ ይባላሉ። አስከሬናቸው ያረፈበት ምድር ላይ የኢሣፓ ጽፈት ቤት ተሰርቷ
፣ ባሌ ጎባ ስትደርሱ Welcome to Bale Goba ከሚለው በስተግራ ታገኙታላችሁ። ታደሰ ይርገጤም የተወረሱ ማሳዎች ለጊዜው በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ቆይተው፣ ባጅት ተመድቦላቸው ይታረሱ፣ የከተማው ቦዘኔ በቀን ሠራተኛነት ይሰራ፣ ቢ
ለገበሬው አንዳይከፋፈ
አሸጥር ነው ብለው ሊያስሩት ሲያሴሩ አምልጦ አዲሰ አባባ ቢገባም አላመለጠም፣ ይዘው ገለውት ካሳቺስ እርሻ ሚኒስተር ጽፈት ቤት በራፍ ጣሉት። እነዚህ ወጣቶች መሥሪያ ቤታቸው እነደተዘጋ ለድህረ ምርቃ አሜሪካ እንዲሄዱ አለቃቸው አመቻችቶላቸው ነበር፤ ሀገራችንን በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትተናት አንሄድም ብለው የቀሩ ናቸው፤ አለቃቸው ዛሬ ከስደት ተመልሰው ሀገር ቤት ይኖራ

በደርጎች ውስጥ ኢሕአፓ ቀውስ በመፍጠሩም ደራሲው ይወቅሳሉ፣ እርሰ በእርሳቸው ለሥልጣን ሽኩቻ ባደረጉት መገዳደልም ኢሕአፓን ተጠያቂ ያደርጋሉ፤ ተጨባጭ ማስረጃ አያቀርቡም፣ በአንድ በህቡዕ በሚሰራ ድርጅት ውስጥ ግለሰቦችን አባ
ናቸው ማለት ይከብዳል፡፡ በደር
ውስጥ የሚታየው በችሎታና በሥራቸው በታወቁና ሻለቃ መንግሥቱ ያሉት ሁሉ ይሁን በሚሉ መካከ
ነበር፤ ኢሕአፓም ደርግም የሚከተሉት ርዕዮተ ዓለም ሶሻሊዝም ነው፤ ከደር
ውስጥ የነበሩት ሊሂቃኑ የኢሕአፓን ሰለ ሶሻሊዝም የሚሰጠውን ትንታኔ ሊወዱት ይችላሉ፣ ግን አባ
ናቸው ማለት እንዴት ይቻላ
? ለምሳሌ የመኢሶን አባ
የሆኑት አቶ አበራ የማንአብ በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃ
መጠይቅ መቶ አለቃ አለማየሁ ኃይሌና እርሳቸው አንድ ቤት እንደሚኖሩ ነው፤ ሰለመሬት ጉዳይ አብረው እንደሰሩ ተናግረዋል፣ ደራሴው የመቶ አለቃ አለማየሁ ኃይሌን ቀደኛ የኢሕአፓ አባ
አድርገው አቅረብውታል። በግልጽ የሚታየውን በዕውቀታቸው በሚተማመኑትና በቲፎዞና በአድርባዮች ስብስብ በሚመሩት በሻለቃ መንግሥቱ መካከ
ያለውን ቅራኔ ከመግለጽ ተቆጥበው ማረጋገጫ በማይሰጡበት ጉዳያ ላይ አተኮረዋል።
ኢሕአፓን፣ ሀገር በማስገንጠል፣ በፀረ-ኢትዮጵያዊነት፣ ከውጪ አገር አበሮ ሀገራችንን በመውጋቱ፣ በገዳሐሪፍና በሞቅድሾ ቢሮች በመክፈቱ ያወግዙታ
፤ ደራሴው ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት መንግሥታችው ወያኔ ኤርትራን ለማስግንጠ
ይዋጋ እንደነበር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይነግሩት ነበር። የወያኔ መስራችም አቦ ስህባት ነጋ ኤርትራን በማስገጠላቸው ጃሎ መገን ሲፎክሩ ይሰማሉ፤ ደራሴው በምን መረጃ ኢሕአፓን አስገጣይ እንዳሉት አላብራሩም ፣ ይህን በታሪክ የሚያስወቅስ ተግባር በኢሕአፓ ላይ ሲለጥፉ ማስረጃ ማቅረብ ግድ ይላቸው ነበር፤ ወያኔን ከታሪክ ተወቃሸነት ለማዳን ሲሉ ለሕብረቤሄር ይታገ
የነበረን ድርጅት አስገንጣይ ማለቱ ማንንም አይሳምንም። ከጥላቻ በመነሳት ብቻ ፍትው ብሎ የሚታየውን ሐቅ ማወላገድ ታሪክ ማስተማር አይሆንም፣። በተጫባጭ ዛሬ የሚታየው ሕዝቡ ወያኔን ፀረ-ኢትዮጵያ እያለ ሲያወግዝ ነው፣ ካለ ወደብ አሰቀረኝ፣ ለም መሬቴን ሸጠ፣ ሀገር ቆርሶ ለባዕድ ሰጠ፣ የዘር ፖለቲካ አሰፋፋ፣ ወገን ከወገኑ አጣላ የሚሉትን ምክንያቶች ይሰጣል፤ ኢሕአፓ ሥልጣን ይዞ ሀገር ሣይመራ ደር
በመፋለሙ ብቻ ፀረ-ኢትዮጵያ ሊሆን ይችላ
? ወይስ ወያኔን ከየታሪክ ተወቃሽነትን ለማዳን ሆን ተብላ ሰሞኑን የቀረበች ናት? ኢሕአፓ በሞቅድሾ ቢሮ አልነበረውም፣ በሱማሊያ በኩ
ከሀገር ወጥተው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሊመሰክሩ ይችላሉ፤ ፤ ከደር
ጋር ተሰልፈው ነፍስ ያጠፉ ጭምር ለስደት ሱማሊያ ሲገቡ ኢሕአፓ ነን ነበር የሚሉት፤ እነሱ ሳይቀሩ ሊመሰክሩ ይችላሉ። በሀገር ቤት አንድ አባባ
ነበር፣ ‘ዲሞክራሲያ’ እንደ ወንጂ ሰኳር በአይሮፕላን፣ በመኪና፣ በአጋሰስ፣ በአህያ፣ በግመ
ተጭና የገጠር ከተማዎችን አዳርሳለች። ነጋዴው መርካቶ የተበተነን ወረቀት ለእርሱ የሚጠቅመው ነገር ያለበት መስሎት ከመንደሩ ይዞት ይመጣል። ብዙ ጊዜ አሰተማሪዎችን ወይም የተማሩ ልጆቹን ያስነብባል። የኢሕአፓ ልሳን መሆኗን ያወቁ አንዷን ቅጽ እንኳን ያነበቡ ኢሕአፓ ነን ማለት ይጀምራሉ። ‘ዲሞክራሲያ’ በግመ
ተጭና ኦጋዴን ለመግባት ማን ይከለክላታ
? የዕድገት በሕብረት ዘማቾችንም አንርሳ፤ ደር
በከተማ ኢሕአፓ ላይ ሲዘምት በሐረር፣ በድሬደዋና በጅጅጋ የነበረው ወጣት የኮበለለው ወደሱማሌ ነው፣ ጥቂት ሱማለኛ ተናገሪ ወጣቶች በምዕራብ ሱማሌ ሰም የሚቀሳቀሱትን ቡዱኖች ተቀላቅለዋል፤ የኤርትራ፣ የትገራይ ወጣቶችም አድርገውታል፤ እነዚህን ነበር ደራሴው ከውጭ አገር አብሮ ሀገሩን ወጋ ብለው ያቀረቡት፤ በዚያን ወቅት መሣሪያ የታጠቀ ቡድን ደርግን እዋጋለሁ ይ
እንደሆን እንጂ ኢትዮጵያን እዋጋለሁ የሚ
አልነበረም። የኢሕአፓን መጨረሻ በዚህ ልቋጨው፣ አንድ ወጣት በኢሕአፓነት ሲፈለ
ከአካባቢው ለሁለት ዓመት ከተሰወረ በኋላ ወደ መንደሩ ይመጣል፣ የዘመዱ ጓደኛ የሆኑ ኦሮምኛ ተናጋሪ በኦሮመኛ ‘ ወራ ከረራ ደጋለሙ’ በቀዬው ላይ ቆሞ የሚዋጋው ክፍ
ነህ? ካሉ በኋላ፤ አዎ ስላቸው ‘ወራኒ ዼሲ ገሊ ኦዼሲ’ ወግተህ ሽሻና አውራ ግባና! ጠላትህን አቁስለህ ገብተህ ታወራለህ፤ ምን ዋጋ አለው ማለታቸው ነው።
ሰለ የመላው የኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) 341 ላይ የመኢሶንና የደርግን ፍቺ መቃረቡን እናያለን፤ የመኢሶን አባላት ኮሎኔ
መንግሥቱ ኃይለማሪያምን እጁን ይዘው፣ የሶሻሊዝምን ሀ ሁ እንዳላስቆጠሩት ዕውቅት ከሥልጣን ይመጣ ይመስል፣ ለመኢሶን አባላት ‘ሰለአገራቸው ወቅታዊ ፣ ወታደራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ገለጣ አደረጉላቸው’ ይሉናል።ከውጤቱ እንዳየነው ሊገላቸው እንዳስፍራራቸው ነው። በዚሁ ገጽ ላይ የመኢሶን አባላት በሀገሪቱ ተበትነው ለሚገኙት አባሎቻቸው ሣያስታውቁ፣ የሱማሌ ጦር ወደ መሐ
ሀገር እየገለገሰ መምጣቱን አይተው በፍረሃት ፈረጠጡ ይሉናል፣ ከአባላቱ አንዱ ብልጣ ብልጡ አሥር ሺ የኢትዮጵያ ብር ይዞ በቦሌ መኮብለሉን አልሸሸጉም፣ በመጽሐፋቸው ውስጥ የሸሸጉን ነገር ቢኖር ግን፣ ሀገር ወዳዱ እያሉ የሚያቆለጳጵሱት ፕሬዘዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪያም የወያኔና የሻዕብያ ሀገር አጥፊ ሽፍቶች ወደ መሐ
ሀገር ሲገሰግሱ አይቶ፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆነ ሠራዊት ከነሙሉ ትጥቁ በትኖ፣ መጠኑን ያልነገሩንን ገንዘብ ዘርፎ፣ ሀገርና ሕዝብ አጥፍቶ፣ አይሮፕላን ጠልፎ ወደ ዙባቤ ሰለጠፋው ያሉን ነገር የለም። ይበልጥ ያተኮሩት በሕይወት ሰለሌሉት፣ እንደ ዱኩላ አድነው ሰለገደሏቸው፣ የፍጥኝ አስረው ሰለረሸኗቸው፣ ገድ
ነው። ሰለ መኢሶን ድርጅት አባላት ያቀረቡት ግንዛቤ ማናቸውን የድርጅ አባላት ይመለከታል፤ ‘የመኢሶን አመራር አባላት ሁሉም በከፍተኛ ደረጃ የተማሩ ይሁኑ እንጅ አገራቸውን በጥልቀት አያውቁም፤’ የደር
አባላት ደግሞ ይበልጥ ሀገሪቱን አለማወቃቸውን ዘለውታል።
ስለወዝ ሊ
መስራቹ ዶክተር ሰናይ ልኬ ብቃትና ስዕብና ጥሩ አድርገው አቅርበውታ
፣ ከሠራዊቱ ውስጥ ብቃት ኖሯቸው ለወዝሊ
አባላንነት የተመለመሉትን ገልጽዋል፣ እርሳቸው የእርሱ ምልም
መሆናቸውን አልነገሩንም፤ ሌሎች ጓዶቻቸውን በሰደድ ድርጅት ሰርጎ ገብነት አጋልጠው ለመንግሥቱ ኃይለማሪያም ግድያ አሣልፈው ሰጥተዋቸዋ
፤ ሰለጓዶቻቸው አሟሟት ያሉት ነገር የለም።
ደራሲው እንዳቀረቡት የአብዮታዊ ሰደደ መስራችም ሊቀመበርም መንግሥቱ ኃይለማሪያም መሆናቸውን ነው። ለምን እንደመሠረቱት በገጽ 345 ላይ ገልጽውታል፣ የዶክተር ሰናይ ልኬን ከወታደሩ ውስጥ በዕውቀት ላቅ ያሉትን ለወዝሊ
መመልመሉ ለሥልጣናቸው አሰጊ ሆኖ ሰለአገኙት መሆኑ ግለጽ ነው፤ ደራሲው አደጋ ካለው ወዝሊ
ወደ ሰደድ ያደረጉትን ሸግግር በለውሳስ አለፍውታል፤ የድርጅቱን ፕሮግራም ማን እንዳዋቀረው አልነገሩንም፤ መቼም በስድስት ወር ሀ ሁ መንግሥቱና ለገሰ አስፋው ሊሆኑ አይችሉም፣ እርሳቸው ቢሸሸንም እኔ ልገራቸሁ፣ ገጽ 354 ላይ ከአሲንባ ከኢሕአፓ እጃቸውን የሰጡ ብለው የአምስት ግለሰቦችን ስም ዝርዝር ጽፈዋል፣ ከነዚህ ውስጥ የሊቀመበሩ የቤተሰብ አባ
ነው የሚባለውን የአያሌው ከበደን ስም ሆን ብለው ዘለውታል። የአብዮታዊ ሰደድን ያዋቀሩት ተስፋዬ መኮንንና አያሌው ከበደ ዋናው ተዋናኞች ነበሩ፤ አያሌው ከበደ በየክፍለሃገሩ እየዞረ በአንድ እጁ የማሌሪድ ልሳን የነበረውን ሪቮሊሽንን ሲያድል፣ በሌላ እጁ የሰደደን ፕሮግራም እያደለ ለድርጅቱ ብሮክራቱን ይመለም
ነበር።
እንደ ደራሲው አቀራረብ በግልቡ ካየነው፣ ሰደድና ማሌሪድ የተለያዩ ድርጅቶች ሊመስሉን ይችላሉ፣ ሰደድ ሲባ
የወታደሩን ክፍ
ስለሚያጸባርቅ፣ የቡርጌሱን ምቾት ለመጠበቅ በስላቅ ማሌሪድ ተቋቋመ፣ በእርግጥ የሥልጣኑን የአንበሳውን ድርሻ ያለው ሰደድ ነበር፣ ሰለዚህ ማሌሪድ የሰደድ ዣንጥላ ያዥ ነበር።
የኢትዮጵያ ጭቁኖች አበዮታዊ ትግ
(ኢጭአት) ከገጽ 357-359 ይህ ድርጅት በተቀሳቀሰበት አካባቢዎች የፈጸማቸው ን እኮይ ተግባሮች ጽፈዋል፣ መታወቅ ያለብት በህቡዕ ከሚቀሳቀሰው ከኢሕአፓ በስተቀር የቀሩት በመንግሥት ዕውቅና የሚሰሩ ናቸው፤ ሰለዚህ ለተፈጸሙት ጥፋቶች ተጠያቂው የራሳቸው መንግሥት ነው። ለምሳሌ በባሌ ክፍለሃገር የተመደቡት የደር
አባላትና የኢጭአት ካድሬዎች እጅና ጓንት ሆነው ሠርተዋል፣ አቆርቋዥ ፣ አደሃሪ ፣ ነፍጠኛ፣ ኢሕአፓ በማለት ማገርና ግድግዳ ሆኖ ሀገሩን አስከብሮ የኖውን የሕብረተሰብ ክፍ
እየመረጡ አጥፍተዋል፣ በጋራ የሚገሉት፣ የሚያስገድሉት አክተመ ፣ አካባቢውም የጅግና መካን ሆነ ፣ ሕዝቡም በየአቅጣጫው ወደ ጫካ ገባ፣ አቅም ያለው ሱማሌ ሄዶ በሱማሌ አቦ ስም መሣሪያ ታጥቆ በጫካ መሽገ፣ በደር
አባሉና በኢጭአት አባላት መካከ
የሥልጣን ሸኩቻ ተፈጠረ፣ ‘የኢጭአት ካድሬዎች ‘መጤ፣ ነፋጠኛ’‘ እያሉ የአማራኛ ተናጋሪውን እንዲባረር ቅስቀሳ እንዳደረጉ’ ፤ ካለደር
አባሉ እውቅና የሚደረ
ነገር የለም። ‘መጤ’ የሚለው ቃ
የመጣው የሸዋው ኦሮሞ ፣ የእስልምና ተከታይ በሆነው ኦሮሞ መሬት ላይ ሰፍሮ በኩ
አራሸነት ያርስ ነበር፤ ከመሬት አዋጅ በኋላ በመሬት ድልድ
ምክንያት በተፈጠረው ግጭት ብቅ ያለ ቃ
ነበር፤ ደራሴው አጋነውታል። በደርግና በኢጭአት መካከ
ቅራኔው ሰፍቶ ኢጭአቶች በየቅጣጫው መኮብላቸውን እናያለን፣ በሐረርጌ በባሌ በአርሲ ክፍለሃገራት የትጥቅ ትግላቸውን ለማድረ
መሰማራታቸውን ጽፈዋል፣ በባሌና በአርሲ ዋቆ ጉቱ ከሚመሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ለመቀላቀ
መረባቸውን መዘርጋታቸውን ገልጸዋል፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የሚሉት ደርጅት የትጥቅ ትግ
የሚያካሄድ በሐረር፣ በባሌና በአርሲ አልነበረም። ዋቆ ጉቱ በባሌና በአርሲ፣ሼክ ኢብራሂም ቢሊሣ በሐረርጌ በሱማሊያ መንግሥት የሚረዳው ‘የሱማሌ አቦ’ ንቅናቄ መሪዎች ነበሩ፤ በእርግጥ ጃራ የኢጭአት አባ
ባሮ ቱምሳንና ሌሎችን እርግጠኛ አይደለሁም፤ ‘ኦሮሚያ’ የሚለው ሰም የተፈጠረው ወያኔ ሀገሪቷን ከተቆጣጠረ በኋላ ነው፤ ጃራ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኦሮሞ ነው፣ ‘ኦሮሚያ ኢስላሚያ’ የሚ
ድርጅት አልነበረም፣ የነበረው በሱማሊያ የሚረዳው የሱማሌ አቦ ድርጅት ነው፣ የነባሮ ቱምሳ ችግር ሊሆን የሚችለው በሱማሌ አቦ ውስጥ ከተሰገሰጉት የሶማሊያ ሰላዮች ነው፤የተማረ ሰው አይፈልጉም፣ የክርሰትና ሃይማኖት ተከታይ ከሆነ በሰላይነት ይጠሩጥሩታል፣ በተለይ ዐርብ ሮብን የማይጾም፤ እነርሱ ያረዱትን ሥጋ የሚበላ ከሆነ በአይን ቁራኛ ይጠበቁታ
፤ መጨረሻው ሞት ሊሆን ይችላ
። እነባሮ ቱምሳን የዘመኑ አማሮች ወይም ዼጤዎች እገምታለሁ፤ ምክንያቱም ከባሩ ቱምሳ ጋር የተገደለው የባሌ ክፍለሃገር ምክት
አስተዳዳሪ የነበረው መገረሣ በሪ ይገኝበታል፤ ባሌን ሲያስተዳድር ከመስኪድ ሄዶ ‘እስላም ያረደው ክርስትያን ያረደው ብሎ የከፋፈሏችሁ አዳሃሪያን ናቸው’ ብሎ በመቀስቀሱ ት
ቅ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር፤ በሱማሌ አባ ውስጥ የሶማሊያ ሰላዩች ካለሆኑ በሰተቀር መሪዎቹ ለኦርቶዶክስ ተከተዮችና ለቤተክርስትያን ት
ቅ ክብር አላቸው። ያም ያለምክንያት አይደለም፤ በኢትዮጵያ ላይ ያዣበበው ሶሻሊዝም ሁለቱንም የሀገሪቱን ሃይማኖቶች ያጠፋቸዋ
ብለው ሰለሚያሰቡ ነው። ደራሲው ‘የኢጭአት ልሳኑ ነፃነት ያሉት’ የአማርኛው ፍቺ ነው፣ ልሳኑ ‘ቢሉሱማ’ ይባ
ነበር፤ በተከታታይ ከሦስት እትሞች በላይ አላወጣም። ኢጭአትን ለማጋለጥ ብለው፣ ሰለ16ኛው ክፍለ ዘመን የግረኝ መሐመድ ወረራ ትንታኔ በመስጠት፣ ሌላ ሰህተት ውስጥ ገብተዋል፣ በመጀመሪያ ግራኝ መሐመድ ቤተክሪያተኖችን፣ የሀገር ቅርጾችን፣ ክርስቲያኖችን አጥፍቷል፣ በወረራቸው አካባቢዎች መሲኪድ አሰርቶ ቁራን እንዲሰበክ አላደረገም፣ ሰለዚህ ሃይማኖት አላስፋፋም። ኦሮሞች ግራኝ መሐመድን እየተከተሉ የወረራ ዘመቻ አካሄዱ፣ አማራውንና ሌላውን ጎሳዎች አባረው የያዙትን አካባቢ ኦሮሞ አደረጉት የሚ
ትንታኔ ሰጥተዋል፣ በአንድ ጎኑ ሰለእስልምና መስፋፋት ይናገራሉ በሌላ ጎኑ ሰለኦሮሞ ቤሄር አመጣጥ ይገልፃሉ ይህ ሁሉ የኢጭአትን ስህተት የመንግሥታቸውን ትክክልኝነት ለማሳየት ነው፤ መታወቅ ያለበት በ16ኛው መቶ የነበረችው ኢትየጵያ የዛሪቱ ኢትዮጵያ ናት፣ ‘’ መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ’’ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም 2005 ዓ ም ከገጽ 207-211 ያሉትን ካርታዎች መመልከት ይበቃል። ያንን ካርታው ላይ ያለውን ሀገር ወሰን አሰከበሮ እሰከዛሬ ያቆየው የአንድ ጎሳ አባ
እንዳልሆነ እናውቀዋለን። የውጭ አገር ታሪክ ጻፊዎች በፃፉት ላይ ተመርክዞ ከትንታኔ መግባቱ ጥቅም የለውም። ሰለግራኝ መሐመድ ከተነሣ በሕብረተሰባችን የሚነገረው አፈ ታሪክ ያሳምነኛል፣ የግራኝ መሐመድን ኢትዮጵያዊነት ይቀበላሉ፣ በቤተክርስትኖችና በምዕመናኑ ላይ ያካሄደው የግ
ብቀላ እንደሆነ ያቀርቡታል፣ ቄስ የነበረው አባቱ እስላም ከነበረችው እናቱ ፍትቶ ሥጋ ፈጽሞ ጥምጥሙ መስሎት ጉፍታዋን ጠምጥሞ ለቅዳሴ በመግባቱ ቄሶች አባቱን በማቋሚያ ቀጥቅጠው ስለገደሉበት ለብቀላ ያደረገው ጦርነት ነው፣ ይባላል። ሰለአማራውና ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሲነሣ ሰለ ቀድሞው ጠቅላይ ሚነስትር መለስ ዜናዊስ የሚነገር ነገር ይኖር ይሆን?
ምዕራፍ 17 ላይ ከገጽ361-396 አገራችን በሶማሊያ መወርሯን ያትታሉ፣ ደር
የሶማሊን ወረራ በማስቆሙ ራሱን ማሣያ አድርጎ አቅርቧል፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሶማሌ ወረራ አዲስ ነገር አይደለም፤ ብዙ ጊዜ ሞክራ ሕዝቡ ባለው መሣሪያ ከሠራዊቱ ጋር ተሰለፎ አሣፍሮ መልሷታል። አሁን ከኢትዮጵያ የተሻለ መሣሪያ ታጥቃለች በማለት የውጭ ሀገር ሠራዊት የሚያስጋብዝ ለመሣሪያ ሀገሪቱን መለወጥ የሚያኮራ አይደለም። ዘይድ ባሬ ኢተዮጵያን የወረረው በቀደማዊ ኃይለሥላሴ ላይ በወታደሩ የተፈጸመው መፈቀለ መንግሥት በእኔም ይሆናልን በመፍራትከራሱ ላይ አቅጣጫ ለማስለወጥ ያደረገው ወረራ ነው፤ የመንግሥቱም ታላላቅ ሰዎችን ጨርሶ ታላቅ መስሎ ለመታየት ያራገበው ጦርነት ነው። ኢሕአፓ በልሳኑ ‘ዲሞክራሲያ’ ‘ዘይድ ባሬና መንግሥቱ አንድ ናቸው’ ያለውን በተግባር አየነው። ገጽ 392 ላይ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት የነበሩት ጂሚ ካርተር ያሉትን እጋራለሁ፣ሶማሊያ ሳትሆን እናንተ ናችሁ ሽብር ፈጣሪዎች ያሉት ትክክ
ነው። የራሱን ቤት ያቃጠለ እብድ ሌላው እብድ የቀረውን ለማቃጠ
ቢመጣ ተወቃሹ ማነው?
ምዕራፍ 18 ላይ የሶማሊያንና የሱዳንን የዘሩትን አጨዱ ብለው ሲያጣጥሉ በጥንታዊቱ ሀገር እርሳቸው ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ያስተዳደሯትን ኢትዮጵያ ከሁለቱም በታች እንድትሆን አመቻችተዋት ለወያኔ ማስረከባቸውን አሁንም አልታያቸውም።
ምዕራፍ 19 መንግሥታቸው ሰለአመጣው የኤኮኖሚ እድገት አንዳንድ ፎቶዎቹን በመለጠፋ አሣይተዋል፤ ዞር ብለው ደግሞ ቀጣይነታቸውን ገምግመው ቢሆን እድገት ማለት ምን እንደሆን ይረዱ ነበር። የሰዎችን ሰዕባዊ መብት መሐከ
ያላደረገ ልማት ሕብረተሰብን አይለውጥም፣ በየኤኮኖሚ እድገት ሊኖር አይችልም፤ ዕድገት ከነፃ አሰተሳሰብ የሚመጣ ወጤት ነው፤ ፍትህ በሌለበት ስዎች በነፃነት ሐሣባችውን በማይገልጹበት ሕብረተሰብ፣ የኤኮኖሚ እድገት ሣይሆን፣ ባርነት፣ደህነት፣ስደት፣ወርደት የመብት ረገጣ ጎልቶ ይታያ
ይህን ደራሴው ከአርባ ዓመት በኋላም ያዩት አይመስልም።
ዛሬ በ2006 ዓ ም ላይ ሆነን ወደኋላ ተመልሰን በ1966 ዓ ም ከነበረበት የሕዝቡ ኑሮ ተሻሽሏ
ወይስ ብሷ
? ደራሲው አቅማቸው የፈቀደውን ያህ
ተመክሮአቸውን አካፍለውና
፣ ግለሰቦች ነገሮችን የሚያዩበት የራሣቸው መነፅር አላቸው፤ አንደኛው መነፅር መጽሐፍ ነው። ደራሴው ‘እኛና አብዮቱ’ ን እንደመነፅር ተጠቅመውበታል፣ ሊመሰገኑ ይገባል። ሆኖም ግን ሀገር ለማስተዳደር ትልቁ መነፅር ሕዝብ ነው፤ አልተጠቀሙበትም፣ ያንን መነፅር የተጠቅሙት ዕምዬ ምኒሊክ ነበሩ።
ታደለ መኩሪያ
tadele@shaw.ca

Eritrean Delegation in Khartoum

Eritrea participates at 37th AU Council of...

President Isaias returns home concluding working...

Electricity and Youth Empowerment: Eritrea’s...

Somali president returns home concluding two-day...

China: Contributing to World Peace and Development