October 19, 2013

እንደሃገር እንነጋገር!

እንደሃገር እንነጋገር!

እንደሃገር እንነጋገር!ኑር ከሰው ኑር ከሃገር ይል ነበር፡ የሃገሬ ሰው፤ ሰው ለሰው መፈጠሩን የሚገልጽ አባባል ነው። በአጠገብህ ካለው መሰልህ ሰው አብረህ መኖር ከቻልክ በመላው ሃገርህ ካለው ሰው መኖር አያቅትህም ለማለት ነው።

የሰው ልጅ ለራሱ መልካሙን እንደሚያስብና እንደሚሰራ ሁሉ ራሱን ለማጥፋትም የዛኑ ያህል ይሠራል። ጥያቄው ባብላጫው ለየትኛው ይሠራል ነው? ሕዝብ እንደ አንድ የሃገር ዜጋ ተሰባስቦ ሲኖር ማሟላት ያለበት በተፈጥሮ የተቀበለው ግዴታ አለበት። መሠረታዊ የሆኑ ፍላጎቶቹን ማሟላት፣ ስብዕናውን ያለማስደፈር፣የሌላውንም ያለመድፈር፣በሌላው ላይ ፍትህ ሲጓደል የእርሱም እንደተጣሰ መቁጠር፤ ትውልድ እንዲተካው ሲያስብም ቅርስ ማስተላለፍም ግድ እንሚለው ማወቅ ከብዙቹ ጥቂቶቹ ናቸው። ያ ሣይሆን ቀርቶ ዜጎች በረሃብ፣ በጦርነት፣በስደት፣ በፍትህ እጦት የሚጎሣቆሉ ከሆነ ሰው አውቆም ሆነ ሣያውቅ ለመልካሙ ሣይሆን ለጥፋቱ እየሰራ ነው። በግብተኝነት መሪዎች ናቸው ለዚህ ሁለ ጥፋት ተጠያቂዎች በማለት የሚያቀርበው ከሃላፊነት የማምለጫ ምክንያት ውኃ አያነሳም፤ ለምን ቢባል መሪ ከሕዝብ ነውና የሚወጣው፤ ሆኖም ወደዝርዝር ሐታታ ከመግባቴ በፊት ለአንባቢዬ ጥያቄ ላቅርብ፤ በኢትዮጵያ ሃገራችን የመልካሙ ሥራ ወይስ የጥፋቱ ሥራ አይሎ ይገኛል? መልሱን ለእናንተ ለተወው።

ከኖርኩት ዘመን ልጀምር፣ ከአርባ ዓመት በፊት የሕብረተሰባችን አመለካከት፣ የተፈጥሮ ሐብታችን አጠባበቅ አሁን ካለንበት በጥልቀት ሲመረመር፣ ሰው ራሱን የሚያጠፋ እንጂ የሚያለማ ተግባሩ ጎልቶ አይታይም ። በሰዎች መካከል የነበረው መከባበር፣ የሃይማኖት ዕምነት፣የቃልኪደን ጽናት እየተሟጠጠ መምጣቱን ያሣያል። የተፈጥሮ ሐብታችንም በቁማር እንደተገኘ ሐብት በአስረሽ ሚቺው የመሰለ የዜግነት ሃላፊነት በጎደለው መንገድ መውደሙ ይታያል። ሰው ራሱ በሰራው ጥፋት ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ተጋብቷል። በቅርቡ ዶክተር በረሃኑ ነጋ ‘ዴሞክራሲና ሁለንታዊ ልማት በኢትዮጵያ’ በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሐፋቸው ውስጥ ሃገራችን ያለችበትን አስጊ ሁኔታ ገልጸዋል። በጥናት የተገኙ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ለናሙና ያህል ያሉትን ኩነቶች በመጽሐፉ ውስጥ አስፍረዋል። የሰው ልጅ ራሱን ከሚያጠፋው ተግባሩ ይልቅ ከሚያለማው ሥራ ላይ ልቆ ቢገኝ እሰየው ነበር፤ ግን አልሆነም። እንዲሆን ምን መደረግ አለበት? ለሚለው መልሱ እንደሃገር ከመነጋገር ሌላ አማራጭ የለውም። ሰው ለሃገሩ ልማትም ሆነ ጥፋት ሃላፊነት አለበት። እያነዳንዱ ሰው ትውልድ እተካባታለሁ የሚላትን ሃገሩን ካልተከባከበ ለተፈጥሮ ሐብቷ መከበር ዘብ ካልቆመ ከዚያ ውጭ የሚሠራው ለጥፋት ነው። በዴሞክራሲ የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች የማይመሩት አስተዳደር የሚሠራው ለጥፋት ነው። በዘፈቀደ በነዝህላልነት በልምድ የሚሠሩ ሥራዎች የሚመሩት ወደ ጥፋት ነው።

ባለፉት ዘመናት ወደ ሥልጣን የመጡት የንገሡና የደርግ ገዥዎች በሩን ገርበብ አድርገው ዘግተው እኛ ነን ሰለሃገር የምንነጋገር እናንተ ያለናችሁን አድርጉ የሚሉ ነበሩ። አሁን በትረ መንግሥቱን የያዘው የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ሕወሃት) እንደሃገር ሳይሆን እንደመንደር እንነጋገር የሚል ነው። ከናካቴው በሩን በደህንነት፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በአጋዚ ጦር ክርችም አድርጎ ባለሃገሩን አላውቅህም የሚል የቅኝ ገዥዎችን መሰል አገዛዝ የሚያራምድ ነው። ይህን በቅኝ ገዠ ቁልፍ የተዘጋውን በር ማስከፈት የምንችለው እንደሃገር ስንነጋገር ነው። ለገዥዎቻችን በር ጠባቂዎች ቀለብ ሰፋሪዎቹ እኛ ነን እነርሱም በአካል እኛን ናቸው። ሕዝብ ካልፈቀደ መሪዎች ነን ባዮች አንዲት ቀን በመንበራቸው ላይ ለቆዩ አይችሉም። ይህ እንዲሆን መፍቀዱ በራሱ ትልቅ ጥፍት ነው። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ራሳችንን ለዘመናት በማጥፋት ሥራ ላይ እንደተሰማራን የሚያሳይ ነው። ስለዚህ ለጥፋቶች ሁሉ ጥፋት ዜጎች ትልቁን ድርሻ እንወስዳለን።ምክንያቱም ጥቂቶች ሃገር እንዲያጠፉ ብዙሃኑ ፈቅደናልና! ሰው ራሱን ለማጥፋት ይሰራል ስል፤ የዜግነተን ግዴታ ካለማወቅ፣ከግዴለሽነት፣ ከፍረሃት፣ራስ ወዳድነት፣አቆራጭ አማራጭ ለራስ መኖር ከመሻትና አርቆ አስተዋይነትን በማጓደሉ ተቀራርበን ያለመነጋገራችን የሃገራችንን ችግሮች በጋራ ለማስወገድ አለመቆማችን ለጥፋት መስራታችንን ፍትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።

በአሁኑ ወቅት ከምንጊዜውም ጊዜ ይልቅ በተሻለ መንገድ ተቀራርብን እንደሃገር ለመነጋገር አመቺ ሁኔታ የተፈጠረ ይመስላል። የቀድሞ ገዥዎቻችን በሓለፈነታቸው ከጥፋት ነፃ ናቸው አንልም። ወያኔ ግን አሣውን ለማጥፋት ውኃውን አድርቀው የሚል ፓሊሲ የሚከተል ነው። ይህን ማን ፈቀደለት እኛው ነን።

የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ሕወሃት) የተለያዩ የጎሣ አባላትን ለቃቅሞ ሃገሪቱ የምትተዳደርበትን ሕገ መንሥት ቀረፆ ኢህአዴግ የሚባል ድርጅት ነው ሃገር የሚመራው አለን። ሐቁ ግን ሕገ መንግሥቱም ኢህአዴግም የፈረስ ዕቃ ናቸው። ጋላቢው የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ሕወሃት) ትግራይን ለመገንጠል ፣ ኤርትራን ለማስገንጠል 1967 ዓ ም የቀረጸው ፕሮግራሙ ዛሬ በመላው ሃገራችን እየተገበረ ነው። ይህ ፕሮግራም ፋሺሽት ኢጣሊያ 1928 ዓ ም ኢትዮጵያን በቅኝ ለመያዝ ያለ የሌለውን ኃይሏን ተጠቀማ ሳይሆንላት ሲቀር የነደፈችው የዘርና የጎሣ ሰነድ ነው። በዘርና በጎሣ ከፋፍሎ ማዳከሙ ለጊዜውም ቢሆን ስርቶላት ነበር።ከሰባ ዓመት በኋላ ወያኔ በጎሣና በዘር መከፋፈሉን መሰሎኒ የጀመረውን ለፍፃሜ ለማድረስ ሃያ ሁለት ዓመት ተቀሳቅሷል ሆኖም ይህ ሰው በሰው የሚደረገው ጥፋት መቆም እንዳለበት እንደሃገር የምንነጋገርበት ወቅት የተቃረበ ይመስላል። ኢትዮጵያውያን እንደሃገር እንዳንነጋገር ያደረገን ፤የወያኔ አብዮታዊ ዲሞክረሲ ርዕዮተዓለም አስተሳሰብና ፖሊሲ የፈጠረው ችግር አይደለም። በሌላ መልኩ የትግራይ ሕዝብ ሕወሃትን ጠላው ወይም ሌሎች ፓርቲዎችን ተጠራጠረ ብሎ ችግሮች በአንድ ሕብረተስብ ክፍል ብቻ ማድበልበሉ ምናልባት አቅጣጫ ማስለወጥ ካልሆነ ፤ ችግሩ አንድና አንድ ብቻ ነው። ያም መላው ሕዝብ የሚጋረው ቸግር ነው። ወያኔ በሥራ ላይ ለማዋል የነደፈው የቅኝ ገዥዎች ሰነድ ነው።

እንደሃገር ስንነጋገር ይህን የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንበር (ሕወሃት) የዘር ፖለቲካ የሚያጸባረቀው ሰነድ ወደቁሻሻ መጣል አለበት። ከዚያ ባለፈ በሕር ቀለም ቢሆን ሰማይ ብራና ሆኖ ብንለቀልቀው ወጤት የለውም። ግለሰቦችን ማውገዙ መግለጫ ማውጠቱ፤ግለሰቦች በሕዝብ ላይ ላደረሱት በደል በሒደት ፍርዱን ይቀበላሉ ። የማናገኘው የተፈፕሮ ሐብታችንና የሚተኩን ልጆቻችን አዕምሮ አጉልፋቶ እየሆነ ነው።ይህ ደግሞ ለባርነት የሚያዘጋጃቸው ነው። እዚህ ላይ የማይቀረውን የሞት ጽዋ ሁላችንም ቀማሾች ነን። ለቀሪው ወገናችን ምን አንተውለት? የሚከፋፍለውን ሠነድ? ምድረበዳ ሃገር? መልሱን ለእናንተ ልተው!
ታደለ መኩሪያ

tadele@shaw.ca

Nationals in abroad conduct various activities

Message of President Isaias to Saudi King

Senior Eritrean delegation held talks with Saudi...

Senior Eritrean delegation on working visit to...

PRESS STATEMENT

Eritrean delegation met and held talks with...