June 29, 2012

አርቲስቶችና ነጋዴዎች በአላሙዲን AESAONE ዲሲ ፌስቲቫል ላይ እንዳይሳተፉ እንጠይቃለን

አርቲስቶችና ነጋዴዎች በአላሙዲን AESAONE
ዲሲ ፌስቲቫል ላይ እንዳይሳተፉ እንጠይቃለን

EthiopianReview.com | የመለስ ዜናዊ አምባገነናዊ አገዛዝ አንጋፋዉን በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን ለማፍረስ የአላሙዲንን ገንዘብ ተጠቅሞ ህሊናቸውን በሸጡ ሆድአደር ወኪሎቹ አማካይነት የሰላም የሆነውን የስፖርት መድረክ በተለመደ የከፋፍለህ-ግዛ ፖሊሲው መጠቀሚያ ለማድረግ በስም አመሳስሎ ሊያደናግር ቢሞክርም በፍትህ አደባባይ ከተረታ በኋላ “AESAONE” የሚል ስም አውጥቶ እኩይ ዓላማውን ለማሳካት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በአላሙዲ አማካይነት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ዓላማቸውን ለማሳካት በገንዘብ እናሸንፋቸዋለን ያሉዋቸውን አርቲስቶች የበዓሉ አድማቂ እንዲሆኑ እና ለተሳታፊነትም በተለያዩ ግዛት ለሚገኙት የወያኔ ደጋፊዎች የጥሪ ዘመቻ ይዘዋል።

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከላይ እስከ ታች በህወሃት ሰዎች ተይዞ ድርጅቱን የአፍሪካ መኩሪያ ያሰኙትን ዕውቀትና ልምድ ያላቸውንና በሙያቸው ከአገር አልፈው በዓለም ዕውቅና ያተረፉ ኢትዮጵያውያን ፓይለቶችን፣ የበረራ አስተማሪዎችን፣ ቴክኒሽያኖችን እና የማኔጅመንት ሰዎችን በማሳደድ የሽያጭ ስራውን ጭምር ለሕንድ እየሰጠ የበርካታ አገር ዜጎችን በከፍተኛ ገንዘብ እየቀጠረ ለህወሓት ሰዎች ግልፅ መጠቀሚያ ሆኗል። በውጭ ጭምር ለህወሃት ሰዎች የፓርቲ ድግስ የነፃ የትኬት ቶምቦላ መስጠቱ ሳያንስ አሁንም የወያኔውን የዲሲው ፌስቲቫል በስፖንሰርነት በመሰለፍ ከአገር ውስጥ ካድሬዎችንና ለበዓሉ ይመጣሉ ለሚባሉ ሁሉ የነፃ ትኬት እየሰጠ የስርዓቱ ወገንተኛና ግልፅ መገልገያ መሆኑን አረጋግጧል።

በዚህ በስፖርት ስም በሚካሄድ ዲያስፖራን የማከፋፈያ ፌስቲቫል ላይ የወገናቸው መከራ የሚታሰባቸው፣ ዛሬ አገራችን የገባችበት ኢኮኖሚያዊ አዘቅትን የተገነዘቡት በተለያዩ ንግድ የተሰማሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ አርቲስቶችና ነጋዴዎች ባይሳተፉም ጥቂቶች ግን እንደሚሳተፉ ለማወቅ ችለናል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች በወያኔው ፌስቲቫል ላይ ከመሳተፍ እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን።

ይህን የወያኔን የከፋፋይ ሴራ የሚቃወም ጥሪ ባለመቀበል በዝግጅቱ ላይ የሚሳተፉትን አርቲስቶችና ነጋዴዎችን እያወገዝን ህብረተሰቡ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ካገራቸውና ነፃነታቸው ይልቅ ሆዳቸውን ያስቀደሙትን ለይቶ ሊያጋልጣቸው ይገባል።

በወያኔ ሆድ አደሮች ሽንገላ ባለመደናገር ክብራችን ከሆዳችን ይበልጣል! ከወገኖቻችን ገዳዮች ጋር አናብርም! በማለት በወያኔው ፌስቲቫል ላይ ሀገረ ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዳትገኙ እናሳስባለን።

በወያኔው ፌስቲቫል ላይ መሳተፍ ማለት ዛሬ በጋምቤላ የአዶልፍ ሂትለርን የግፍ ተግባር በሚያስታውስ መልኩ ንፁሃንን ገሎ ሬሳቸውን በቤንዚን ያቃጠለውን፣ ዜጎችን በገዛ አገራቸው ዘራቸውን እየቆጠረ አማራ ይውጣ ሲል ከጉራ ፈርዳ በ70 ሺህ የሚቆጠሩትን ያፈናቀለውን፣ ፋሽስት ኢጣሊያ እንዳደረገው በጎንደር ንፁሃንን ገድሎ ሬሳቸውን መንገድ ለመንገድ በመኪና ለጎተተው፣ የታሪክና የሀይማኖት ቅርሳችንን ዋልድባን በልማት ስም የሚያፈርሰውን፣ የዕምነት ነጻነታችን ይከበር ያሉ ሙስሊም ወገኖቻችንን በአርሲ አሳሳ በመስጊድ ዉስጥ የገደለና የሙስሊሙን ህብረተሰብ ህጋዊ ጥያቄ ወደ ጎን አድርጎ አሸባሪ ሲል ስም የለጠፈውን፣ ጋዜጠኞችን፣ ነፃ አሳቢ ዜጎችንንና ተቃዋሚዎችን አስሮ የሚያሰቃየውን፣ ኦሮሞነትን ወንጀል አድርጎ እስር ቤቶችን በኦሮሞ ወገኖቻችን እያጣበበ ያለውን በኦጋዴን በወልቃይት፣ በአፋር ወገኖቻችን ላይ በጅምላ ግድያና በዘር ማጥፋት ወንጀሉ የገፋበትን በአጠቃላይ የስርዓቱን የመብት ረገጣና የአገር ሀብት ዝርፊያ መደገፍ ነው ብለን እናምናለን።
ስለዚህ አርቲስቶችም ሆኑ ነጋዴዎች እንደነፃነት ወዳድ ወገኖቻችን ሁሉ የወያኔውን የዋሽንግተን ዲሲ ከፋፋይ ፌስቲቫል አንሳተፍም በማለት በገንዘብ ማንንም ባሪያ አድርገን እንገዛለን ላሉት እብሪተኞች ትምህርት ልንሰጣቸዉ ይገባል ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Boycott TPLF Task Force
boycott.tplf@gmail.com

Remarks by Ms. Elsa Haile, Director International...

High level Eritrean military delegation delivers...

President Isaias Afwerki and Prime Minister Abiy...

President Isaias returned home concluding working...

President Isaias held talks with President Al Sisi

President Isaias Afwerki on working visit to Egypt