April 18, 2013

ማስተማር ወይስ ማደናገር?

ማስተማር ወይስ ማደናገር?

ማስተማር ወይስ ማደናገር?ስለ ሙስሊም ኢትየጵያውያን መሪዎች ለኢሳት ገንዘብ ማሰባስብ ዝግጅት ላይ መገኘትና ስለታማኘ በየነ የዋህ አነጋገር ተክለማካኤል አበበ ለአቀረበው ጹሑፍ ማስተባበያ የቀረበ ነው።

ወደ ዘርዝር ሐሣቡ ከመግባቴ በፊት ስለአንድ ገጠመኝ ጀባ ልበላችሁ፤ ጊዜው ቢረዘምም አይረሳም፤ በ1969 ዓ ም ነበር። ሻለቃ ዮሐንስ ምስክር ብቻውን በምኒልክ ቤተ መንግሥት የከተመውን የደርግ ፣ የካድሬ ጎራ የጦር ሜዳ ቀጠና አድርጓት መዋሉ ምንጊዜም ይወሳል። በዕለቱ እምድር ቁና ትሆናለች፤ ሻለቃ ፣ኮሌኔል፣ ጅንራል ፣ ሊቀመበሩ ሳይቀሩ ከታንክ ውስጥ እንደተጠለሉ ይነገራል። የካድሬው መንጋማ እንደ አሻሮ ተቆላ ተብሎለታል።

ታዳንስ አንድ ሻለቃ ዮሐንስ ምስክርን ኮፍጣና ወታደር መሆኑን የሚያውቅ የዘብ ሃለፊ ሻለቃ ባሻ እሱ መሆን አለበት በማለት ሁኔታውን ያጣራል። እርሱ እንደሆነ ይደርሰበታል። ‘ሻለቃ ዮሐንስ ምስክር ነው! ተረጋጉ!’ እያለ ከአንዱ ማዕዘን ወደሌላው ይሯሯጣል። ምድረ ሻለቃ፡ ኮሌኔል ጅንራል ፡ የደርግ አባል፣ የአብዮት አራማጅ ካድሬ ሳይቀር፤ በየጠረጴዛው፣ ቁም ሳጥኑ ተሸሸጓል። ሊቀመበር መንግሥቱም በታንኩ ውስጥ ኩሼ ብለዋል። የዘብ አላፊው ሻለቃ ባሻ፤ ሻለቃ ዮሐንስ ምስክር ብቻውን ይህን ሁሉ ቀውጤ እንደፈጠረ ሲያውቅ እራሱ ከሻለቃው በላይ ጀግና ለመሆነ ቃጣው። ወታደራዊ ሰላምታ እየሰጣቸው ሁሉንም ከተሸሸጉበት እንዲወጡ አደረገ። ‘አንዱ ሻለቃ ዮሐንስ ምስክር ነው እንደብርጌድ የዘመተብን ደርሸበታለሁ በማለት ተኩራራ፣ ልቡንም አሣበጠ። ከዚያ በኋላማ ማን ይቻለው? የደርጉም ሊቀመበር የሻለቃነት ማዕረግ ሰጡት። ከእርሳቸው በመለስ ለማንም አልታዘዝም አለ። በደርግ ጽፈት ቤት ግቢ እንደልቡ ይፏልል ጀምረ። ጸረ አበዮተኛ እያለ መግደሉን አጧጣፈ።ለትንሹም ለተልቁም መሣሪያ መምዘዙን ጀመረ። ቀደም ያሉት ካፈጸሙት ግድያ በልጦ ለመገኘት የብዙሃንን ነፍስ አጠፋ። ለእርሱ ግን መልካም ሥራ ይመስለው ነበር። ሌሎችም እንደሱ ሰው መሆናቸው ተረሳው። ኮሌኔል አጥናፉ አባተን እርሱ እራሱ እደገደላቸው ይናገራል። የበላዮቹን በሥልጣናቸው እየገባ በእርሱ ብሶ በሥልጣኔ ገባችሁብኝ እያለ በራ ከረዩ ይል ጀመር። እንዲህ ነው ለሕግ ያለመገዛት እንደፈለጉ መፏለል።
ሁለተኛው በቅርብ የሆነ ነው።ነፍሳቸውን ይማረውና ዶክተር ዮናስ አድማሱ ወንደማቸው ዮሐንስ አድማሱ ስለታዋቂው ጻሐፊ ዮፍህታይ ንጉሴ ሥራዎች ጀምረውት የነበረውን ከፍፃሜው ደርሱ ለሕዝብ ይቀርባል።ሥነሥረዓቱን የመሩት ግለሰብ ያሳዩት የሥነምግባር ግድፈት ትዝብት ላይ እንደጣላቸው ተቺው ጠቀስ አድርገው አልፈውታል። መነሻቸው ለሥራው ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና ለማቅረብ ነበር።ርዕሳቸውም ያተኮረው ‘ ሦስቱ ዮዎች’ ላይ ነበር። ዮናስ አድማሱ፣ ዮሐንስ አድማሱና ዮፍህታይ ንጉሤ። የነዚህን ታላቅ ዮዎች በመድረክ ላይ ያስተዋውቅ የነበሩት ግለስብ ባለታሪኮቹ በሕይወት ሰለሌሉ እራሳቸው የታሪኩ ፈጣሪ ሆነው መቅረባቸው ነው ያናደዳቸው።ይህ ዓይነቱን መጥፎ ባህል መቼ ነው የምናስወግደው በማለት ነበር ስሜታቸውን የገለጹት።

ልጅ ተክለማርያም አበበ ጹሑፉን በቅርብ በሚያውቀው በሰባአዊ መብት ተከራካሪ ታማኝ በየነ ይጀምራል።ይሄውም የክርስቲያኑ ባዓል ሲከበር የዕስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን አለመከበሩን ታማኝ በየነ በመናገሩ እንደየዋህነት ቆጥሮታል። አበው ሲተርቱ ‘ከጥምጥሙ ይቅደም መማሩ’ ይላሉ።

በ1966 ዓ ም ነበር። የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት የተከበሩ እንደልካቸው መኮንን ነበሩ። በአዲስ አበባ ከተማ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖታችን ተገቢውን እውቅና ይሰጠው ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣሉ። መሳ ለመሳ የክርስትና ሃይማኖት በሰልፉ ላይ ነበር። በወቅቱ የ ቀ ኃ ሥ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዋናኛዎቹ ሰልፉን አስተባባሪዎች ነበሩ።ጥያቄው የፍትህ መሆኑን ይረዳሉ። የኢትዮጵውያን ተማሪዎች ከሚደነቁበትና አክብሮት ከሚቸርበት ተግባራቸው አንዱ ወግተኛ አለመሆናቸው ነው። አቶ ተክለሚካኤል አበበ በእርሱ አስተሳሰብ የአቶ ታማኝን የዋህነት ሲገልጽ ፣ብልህነቱ ስለፍትህ የማያውቁ እሲኪያውቁ ቆሞ ያለመጠበቁ ይሆን?።

ሁለተኛው ደግሞ ለኢሳት ለሚደረገው የገንዘብ አሰባሰብ ዝግጅቶች ላይ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መድረኩን ተቆጣጠሩት ፖለቲካውንም ይቆጣጠሩታል የሚል ሥጋት ነው። ልጅ ተክሌ በመላ ምት ላይ ተሞርክዞ ስለ ዘጠና ሚለዮን ሕዝብ ትንተና አይስጥም፤ ነውር ነው። እንዴት ነውር እንደሆነ ወርድ ብዬ አሣያለሁ።

ልጅ ተክሌ ጠላት ወዳጅ ከሚያከበረው ከአበበ ገላው በኢትዮጵያን ስሙ ሲጠራ የማይውለው ታማኝ በየነን አጅብህ በትልልቅ የአሜሪካና የካናዳ ከተማዎች በመድረክ ላይ ሰለታየህ እነርሱን ነህ ማለት አይደለም። የልጅ ተክሌንም ሃይማኖት የጠየቀ አልነበረም። ተክሌ ከሃይማኖቱ በፊት ሰው መሆኑን የኢሳት ሰዎች እንደሚያውቁ እረዳለሁ። እስልምና ተከታይ ወንድሞቻችንም ከሃይማኖታቸው በፊት ሰው መሆናቸውን አይዘነጉም። የሰው ልጅና ፍተህ ሊነጣጠሉ ስለማይችሉ ለፍትህ የሚታገል ሁሉ ሰው ለመሆኑ የሚታገል ነውና ዘር፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ ፣ሞያ ወዘተ ሰው ከሆንን በኋላ የሚመጡ ናቸው። ለልጅ ተክሌ ይህ ይጠፋዋል አልልም፤ በኮታ እንደ ዘር ፓለቲካ ሃይማኖትን ለመመድብ መሞከር በአሁኑ ጊዜ የእስልምና ተከታዩን ወገናችንን የፍትህ ጥያቄ ዳር እስከ ዳር ማጥለቅለቁን ያለማውቁን ያለማቁ ይመስላል።

እንደሻለቃው ባሻና እንደመድረክ አስተዋዋቂው ከዚህም ከዚያም ተሯርጠው ስለነገሩ ጥቂት ካወቁ በኋላ በድንገት በአጋጠሚ ራስን አንድ ቦታ አስቀምጦ ከሌሎች ጋር መላተሙ አይጠቅምም። ይህ ድርጅት እቀፉ ያንን ሃይማኖት አትቀፉ ፣ እንዲህ አድርጉ ለማለት አንተ ማነህ? የሚል ጥያቄ ያጭራልና ከወዲሁ ሰብሰብ ማለቱ አይከፋም። የቁጥጥር ኮሚቴ በኢሳት ውስጥ ይቋቋም ከሆነ መቀበልም ያለ መቀበልም የቦርዱ ነው።ያስተምራል ወይስ ያደናግራል ምርጫው የእነርሱ ነው።

ከዮፍህታይ ንጉሤ ስንኝ አንድ፣ ለመንገድ፤
ለጌሾው ወቀጣ አንደ ሰው አልመጣ፤
ለመጠጡ ጊዜ ከየጎሬው ወጣ።
ምስጋና ይግባቸው ለሦስቱ ‘ዮዎች’ ብዙ ከዚህ እንማራለን።

ታደለ መኩሪያ
tadele@shaw.ca

Cultural performances in connection with...

Eritrean Television and Russia Today (RT) sign...

Eritreans in Cairo celebrate Independence Day...

Senior Eritrean delegation on working visit to...

Africa World Heritage Day observed

Ambassador Semere Russom holds talks with...