January 29, 2013

ሕወሓት የመሰንጠቅ አደጋ ተጋረጠበት

ሕወሓት የመሰንጠቅ
አደጋ ተጋረጠበት

ሕወሓት የመሰንጠቅ አደጋ ተጋረጠበትአውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) – በኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ውስጥ ወሳኝ ድርሻ ያለው ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከአስራ አንድ አመት በፊት ያጋጠመው አይነት የመሰንጠቅ አደጋ ሰሞኑን እንደተጋረጠበት የአውራምባ ታይምስ ምንጮች ከአዲስ አበባ ገለጹ፡፡ ከአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በድርጅቱ አንጋፋ ታጋዮችና በብአዴን አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋ በመሄዱ አሁን ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት የአውራምባ ታይምስ ምንጮች በህወሓት ውስጥ አንጋፋ የድርጅት አባላትን የሚያወግዝ ቡድን በአዲስ አበባና በመቀሌ ለሚገኙ የህወሓት አባላት ደብዳቤ ማሰራጨቱን መረጃዎቹ ጠቁመዋል፡፡

ይህ ለአባላት የተበተነውና በትግርኛ ቋንቋ የተጻፈው በራሪ ወረቀት አባይ ጸሐዬ፣ ስዩም መስፍን፣ ጸጋይ በርሄና ሌሎች የህወሓት አንጋፋ አባላትን ተጠያቂ ከማድረጉም በላይ የህወሓት ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ያትታል፡፡ ‹‹መለስ ህወሓትንም ጭምር ገድሎ ነው የሞተው›› የሚል አመለካከት እንዳላቸው የሚነገርላቸውና በድርጅቱ አባላት ዘንድም እስካሁን ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው አንጋፋው ታጋይ ስብሀት ነጋን የሚኮንነው ይህ ደብዳቤ ማን እንዳዘጋጀው እስካሁን የታወቀ ነገር ባይኖርም እነዚህ የአውራምባ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ከዚህ ደብዳቤ ጀርባ ወጣት የህወሓት አመራሮችና አቶ በረከት ስምኦንን የመሳሰሉ የብአዴን አባላት ሊኖሩ እንደሚችሉ ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ቀደም ሲል በድርጅቱ ውስጥ ይህ አይነቱ አደጋ ሲያጋጥም አቶ መለስ በክራይሲስ ማኔጅመንት ክህሎታቸው እንደተወጡት የሚገልጹት ተንታኞች ዛሬ አቶ መለስ በሌሉበት ሁኔታ ግን መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

ዝርዝር መረጃውን እንደደረሰን እናቀርባለን

Eritrea participates at 33rd ordinary AU summit

Report – ሃገራዊ ሽማግለ ኤርትራውን ዓ/ብሪጣንያ...

Interview of President Isaias Afwerki with...

Official commemoration of Operation Fenkil

President Isaias laid wreath at Martyrs Monument

Press Statement on US Travel Ban